ለኢትዮጵያ ባህላዊ ብልጽግና
Ethio-diaspora
ለሙዚቃ፡ ፊልም፡ ተዋናኝነት፡ ድርሰተ ምጻህፍት፡ ድርሰተ ፊልም፡ ስፖርት
Ethio-diaspora ክብር ይሰጣል!
ስለ እኛ
Ethio-diaspora ለኢትዮጵያ ባህላዊ ትንሳኤና ፡ የስነጥበብ ስፖርት ድርሰትና ፊልም ክብር ለመስፋት፡ በኢትዮጵያና Texas, Atlanta, Dalas, Washington, New york, በሚኖሩ ብዙ ክቡራን ኢትዮጵያውያን ደራስያን፡ ተዋንያን፡ ሙዚቀኞች፡ ስፖርታውያንና፡ ታዋቂ ሰዎች የተመሰረተ ኣለማቀፍ ማህበር ነው። በየኣመቱ ክብር የሚሰጥና፡ በተለያዮ የኣለም ከተሞች ብክብር የሚከበር ''Ethio-diaspora Award '' ለኣሽናፊዎች ያደርሳል። በተጨማሪም ለነዚህ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ታሪካዊ ክብርና፡ የማይበርስ ሃወልት በማሰብ፡ ሰፊ መዘክር ቤት '' Museum'' ለመስራት የተቓቓመ ማህበር ነው።
ኣላማችን
ለበየግዜው ሳይደክሙ ለኢትዮጵያ ክብር፡ ባህል፡ ትምህርት ዝና፡ በየመድረኩ፡ ድንቅ ስራ በመስራት፡ ኩራት ለኢትዮጵያና ህዝብዋ የሆኑ ጀግኖች፡ የምስጋናችን ክቡር ሽልማት በየኣመቱ እያደረስን፡ ህያውና ዘላቂ የባህል መዝክር ቤት መመስረት ነው።
ደስታችን
ጀግኖቹን የማያስከብር ህዝብ ፡ ኣዳዲስ ጀግኖች ኣየገኝም። ጀግኖቻችን በዚህ መልክ በማስከበር፡ ብዙ ጀግኖች ማግኘት፡ ብልጥ ደስታችን ነው!
“ ኢትዮጵያ ብዙ የሰውና የባህር ጸጋ የታደለች ብልጥ ኣገር ናት። ጸጋዋን እንከባከብ ”
ዶር. ኣስረስ መንገሻ